بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡[1]
[1] የመክፈቻይቱ ምእራፍ የቁርኣን በላጭ ሱራ ነች። ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ. ለአቢ ሰዒድ እንዲህ አሉ፡- “ከቁርኣን ሱራዎች ውስጥ በላጩን አሳውቅሃለሁ እርሱም አልሃምዱ ሊላሂ ረቢል ዓላሚን- ነው።" [ቡኻሪ ዘግበውታል]።
الفاتحة
Read Surah Al-Fatihah in Amharic (الفاتحة) with Arabic text, Amharic translation, and audio recitation. Chapter 1 of the Holy Quran, 7 verses — free online.
Quran in Amharic · all 114 Surahs
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡[1]
[1] የመክፈቻይቱ ምእራፍ የቁርኣን በላጭ ሱራ ነች። ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ. ለአቢ ሰዒድ እንዲህ አሉ፡- “ከቁርኣን ሱራዎች ውስጥ በላጩን አሳውቅሃለሁ እርሱም አልሃምዱ ሊላሂ ረቢል ዓላሚን- ነው።" [ቡኻሪ ዘግበውታል]።
ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤
ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ
مَٰلِكِ يَوۡمِ ٱلدِّينِ
የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡
إِيَّاكَ نَعۡبُدُ وَإِيَّاكَ نَسۡتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
ٱهۡدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ
ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡
صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنۡعَمۡتَ عَلَيۡهِمۡ غَيۡرِ ٱلۡمَغۡضُوبِ عَلَيۡهِمۡ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ
የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡ [1]
[1] ኣሚን የምትል ቃል በሶላት ውስጥ እዚህ ትባላለች፤ እንደውም ድምጽ ከፍ በምደረግበት ሶላት ውስጥ ጀማኣው በአንድነት ድምጽ ከፍ ተደርጎ ማለት ያስፈልጋል። ግን እሷ ከፋትሃ አይደለችም።
Al-Fatihah
Play